ሀገሬ ቲቪ

በተመራጭነታቸው ሁለተኛ ደረጃን የያዙት የኢትዮጵያ ምግቦች

የአሜሪካ አንዷ ከተማ የኾነችው ሳንዲያጎ የኢትዮጵያ ምግቦች የሚዘወተርባት ከተማ መኾኗን ጥናት አመላከተ።

ተወዳጅ ኾነዋል የተባሉት የኢትዮጵያ ምግቦች ሽፋን በከተማዋ 4 ነጥብ 8 በመቶ ኾኖ ተመዝግቧል።

ይህም ከፖላንድ ምግቦች በመቀጠል የኢትዮጵያ ምግቦች በተመራጭነታቸው ሁለተኛ ደረጃን እንዲይዙ አስችሏል።

የየት ሀገር ምግቦች በየትኛው ከተማ ብዙ ተጠቃሚዎች አሏቸውን የሚለውን ለመለየት በመላ አሜሪካ በተመረጡ 785 ሪስቶራንቶች ላይ ጥናቱ እንደተደረገ ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-01-31