83ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር የምስረታ በዓል በተለያዩ ሁነቶች በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ አከባበር ላይ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በዓሉ "አምራች ፤ ዘማች የአገው ፈረሰኞች ማህበር "በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የአገው አባቶች ከሌሎች አባት አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚከበር በዓል ነው።
በዮሴፍ ከበደ
2023-01-31
