በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብርናው ዘርፍ ሀገሪቱ ለምታደርገው ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግር የጀርባ አጥንት በመሆኑ የግብርና ምርምር ማዕከላትን አቅም ማሳደግ እና በቴክኖሎጂን ማዘመን እንደሚገባ አሳስቧል።
ቋሚ ኮሚቴው ሰሞኑን በስድስት የግብርና ምርምር ማዕከላት ድንገተኛ የመስክ ምልከታ ማድረገ ታዉቋል።የምርምር ማዕከላትን ማዘመን እና የሰው ኃይል አደረጃጀታቸውን ማጠናከር ካልተቻለ ግብርናን ውጤታማ ማደረግ እነደማይቻል ጠቁሟል ቋሚ ኮሚቴው፡፡
የግብርና ምርምር ማዕከላት የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራ ሊወጡ በሚችሉበት አቋም ላይ መገኘት አለባቸውም ተብሏል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-01-31
