ሀገሬ ቲቪ

የብሪታኒያ ኢኮኖሚ ትንበያ

የብሪታኒያ ኢኮኖሚ በ2023 በ0.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ተንብዩአል። የኑሮ ውድነት በበሪይታኒያዊያን ዘንደ ፈተና እየሆነ መምጣቱን የጠቆመው ተቋሙ ይህ የብሪታኒያ ኢኮኖሚ አደጋ ላይ እንዳለ ማሳያ ነው ብሏል ።

የገንዘብ ተቋሙ በሪፖርቱ የብሪታኒያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በተያዘው አመት ብቻ በ0.3% ከማደግ ይልቅ ይቀንሳል ብሏል።

በአንጻሩ 190 አባል ሀገራትን ያቀፈው አይኤምኤፍ በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት የዋጋ ንረት እየቀነሰ እንደሚሄድ በሪፖርቱ አመላክቷል።

የአይ ኤም ኤፍ ዋና ኢኮኖሚስት ፒየር ኦሊቪየር ጉሪንቻስ በ2022 ብሪታኒያ በ4.1% እድገት እንደነበራት ገለጸው በ2023 ግን እንደሚቀንስ መተነበዩ ለብሪታኒያ አሉታዊ ወጤት ነው በለዋል።

የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ በብሪታኒያ ፈታኝ የሆነ የኢኮኖሚ አካባቢ እንዳለን የሚያንጸባርቅ ነው ሲሉም አክለዋል ። ብሪታኒያ አሁን ላላችበት የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በከፍተኛ ሁኔታ የኃይል ዋጋ መጨመር እና የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ከፍተኛ ጥገኛ መሆን በመክንያት ተጠቅሷል።

ብሪታኒያ ከአህጉራዊው ህብረት ከወጣች በኋላ የተለያዩ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ወጥንቅቶችን አሳልፋልች ። ከቅርብ አመታት ወዲህም ከብሪታኒያ ፓርላማ በተለያዩ ምክንያቶች ገለል ያሉ ፖለቲከኞች ቁጥርም ስድሳን ተሻግረዋል ።

የሪሽ ሱናክ መንበር ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የስልጣን ተጠያቂነትን አሰፈናለሁ በማለት የብሪታኒያ የገቢ ኦዲተር እና የፓርላማ አባል ናዲም ዛሃዊን ከስልጣን ገለል አደርገው ክስም መስረተዋል ።

ተንታኞች እንደሚሉት የብሪታኒያ የኢኮኖሚ መንገራገጭ የሚጀምረው የሃገሪቱ ገቢ በአገባቡ ካለ መሰበብ የተነሳ ነው ሲሉ ይሞገታሉ ።

የእንግሊዝ ባንክ አስተዳዳሪ የሆኑት አንድሩ ቤይሊ የኃይል ዋጋ እየቀነሰ ሲሄድ የዋጋ ግሽበት በዚህ ዓመት በፍጥነት ይቀንሳል ሲሉ ተናገርዋል ።

ነገር ግን ብሪታኒያ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳይከሰትም አስጠንቅቀዋል። ለአለም የኢኮኖሚ ጭንቀት ተጨማሪ መንሳኤም የሆነው የሩሲያ የክሬን ጦርነት ዳፋ ለብሪታኒያ መትረፉን ማሳየ ነው ተብሏል ።

አይ አይ ም ኤፍ እንደሚለው ከፍተኛ የሆነው የወለድ መጨመር፣ የግብር መጨመር እንዲሁም የሃይል ዋጋ መጨመር እንግሊዛወያኑን በእጀጉ አማሯል ።

2010 ጀምሮ የብሪታኒያ ኢኮኖሚ ከፈረንሳይ፣ ከጃፓን እና ከጣሊያን እኩል እያደገ የነበረ ሲሆን በ2016 ደግሞ ከጀርመን ጋር የተሰተካከል ኢኮኖሚ መምራት ችላም ነበር።

አዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስቴር ስልጣንን ከተቆናጠጡ ሶስት ወር አልፏቸውል ። ብሪታኒያ በአውሮፓ እንዲሁም በአለም የኢኮኖሚ ሚዛንን አስጠብቃ እንድተቆይ ያስችሉ ይሆን ቀጣዩ ስልጣን ጊዘያቸው የሚያሳየን ይሆናል ።

ሃገራት ከአይ ኤም ኤፍ የኢኮኖሚ ቁጥር ትንበያ ውጪ የሚያዝ የሚጨበጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለዜጎቻቸው ሊተገብሩ ይገባል።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-31