ሀገሬ ቲቪ

የጤና ሚኒስቴር የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በምዕራፍ ለመጠገን አቅድ መያዙን የጤና ሚኒስቴር አሳወቀ፡፡

ተቋሙ የወባ ወረርሺኝ በ 11 ክልሎች መከሰቱንም ባቀረበው የሰድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ላይ ገልጿል ።

የጤና ሚንስቴር ለጤና፣ ማህበራዊ ልማት ፣ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርትን ዛሬ አቅርቧል ። ቋሚ ኮሚቴው የቀረበውን ሪፖርትም አድምጧል ።

ኮሚቴው ባደርገው የመሰክ ምልከታ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማትን ተመለክቷል ። ኮሚቴው በጦርነቱ ጉዳት የደርሰባቸውን የጤና ተቋማትን ለመገንባት የጤና ሚንስቴርን ዝግጁነት ጠይቋል።

የጤና ሚንስትሯ በበኩሏ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ስራ ለማስጀመር እየተደረጉ ያሉ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል ።

በተያዘው አመት በወረርሺኝ መልክ ከተከስቱ በሽታዎች መሃከል የ ወባ በሽታ አንዱ ነበር ። ሚንስቴሩ በሪፖርቱ የወባ ወረርሺኝ ከ ቤኒሻንጉል ክልል ወጪ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች መከሰቱ ተገልጻል ።

ቋሚ ኮሚቴም በዚህን መጠን የተከሰተውን የወባ ወረርሺኝ ለመከላከል ስለተወሰወሰደው እርምጃ ጥያቄ አንስቷል ። የጤና ሚንስቲሯ በተነሳው ጥያቄ ላይም ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ባቀረበው ሪፖርት ጥሩ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ክፍተት የታየባቸው ስራዎች በቀጣይ በትኩረት እንዲሰሩ አጸኖት ሰጥቷል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-02-01