ሀገሬ ቲቪ

የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር ዕግዱ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያለው ተጽዕኖ

በአዲስ አበባ ከተማ የዜጎችን ሕይወት ከሚፈትኑ ጉዳዮች አንዱ ነው የመኖሪያ ቤት እጥረት። በሚሊየን የሚቆጠር ብርም በቤት ሽያጭ ዘርፍ ላይ ይዘዋወራል።

ታዲያ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ቤት ሽያጭን ለመከላከል በማለት የከተማዋ አስተዳደር በቤት ሽያጭ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከኅዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ "ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር" በጊዜአዊነት እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ይህ ውሳኔ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ አለው ወይ? ስንል ለጉዳዩ ቀረቤታ ያላቸውን ባለሙያዎችን አናግረናል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶ/ር አረጋ ሹመቴ ውሳኔው መንግሥትን ገቢ ከማሳጣት የሚጀምር መሆኑን ገልጸዋል።

የንብረት ዋጋ ትመና እና አስተዳደር ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ አዱኛቸውም በሀገሪቱ በሕጋዊ መንገድ የንብረት ሽያጭ እና ልውውጥ በስፋት ስለማይደረግ መንግሥት ማግኘት የሚገባ ከፍተና ገቢ ሳያገኝ ይቀራል ብለዋል።

ሀገሪቱ ከሚገጥማት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት 43% የሚሸፍነው ከቤት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚመጡ የዋጋ ንረት በመኾኑ መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጤን ተጠቁሟል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-02-01