ሀገሬ ቲቪ

የፖፕ ፍራንሲስ ጉብኝት በአፍሪካ

በሽብርተኝነት እና አለመረጋጋት የበዛባት አህጉረ አፍሪካ አሁን የሰላም እንግዳዋን እየተቀበለች ነው። የካቶሊኩ ሊቀጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በርካታ በአህጉሪቱ በርካታ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እንደሚኒሩባት በሚነገርላት ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ገብተው የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።

ከሀገሪቱ ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ 100 ሚሊዮን የሚሆኑት የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። ከጠቅላላ አማኒያን ውስጥ 40 በመቶዎቹ እንደማለት ነው።

ፖፕ ፍራንሲስም ኪንሻሳ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማኒያንም በአደባባይ እንኳን ደህና መጡ ብለዋቸዋል።

ይህ የሊቀጳጳሱ ወደ አፍሪካ ያደረጉት 5ተኛው ሀዋርያዊ ጉዞ ነው፤ እኚሁ የካቶሊክ አባት የአሁኑን ጉዟቸውን የሰላም ተዕኮ ሲሉ ጠርተውታል።

ሰላም እና ዕርቅን ለማስፈን አልመው የተነሱት ፖፕ ፍራንሲስ ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ውጪም ሰኡዳን ሌላኛዋ መዳረሻቸው ናት።

በኪንሻሳ ከፕሬዚዳንት ፍሊፕ ሺስኬዴ ጋርም ተገናኝተዋል። ይህች ሀገር እና ይህች አህጉር መከበር እና መደመጥ ይገባቸዋል፤ ካጫናዎች ሊላቀቁ እና የተሻለ ትኩረትን ሊያገኙ ይገባል።

ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ከአፍሪካ ላይ እጃችሁን አንሱ፤ የአፍሪካ ማነቆ ሊቆም ይገባል። አፍሪካን እናስብልሻለን እያላችሁ የምትበዘብዟት እና የምታራቅይቷት አህጉር አይደለችም። አፍሪካ የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን ትችላለች ብለዋል።

ፍራንሲስ አክለውም እንዲህ አሉ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዘላቂ ጉዳት እያደረሰ ያለው የኢኮኖሚ ቅኝ አገዛዝ ነው።

ይህች ሀገር በጅምላ የተዘረፈች፣ ከግዙፉ ሀብቷ በቂ ተጠቃሚ ያልሆነች ናት ሲሉም ተደምተዋል።

የተትረፈረፈ የማዕድን ሀብ ፀጋን የታደለችው ዲሞክራቶክ ኮንጎ በዓለም ላይ ካሉ ሀገራት ውስጥ ስሟ በድህነት መጠቀሱ የሚያስቆጭ እንደሆነም አንስተዋል።

እንደ የዓለም ባንክ መረጃ ከሆነ ሁለት ሦስተኛው የኮንጎ ሕዝብ በቀን ከ2.15 ዶላር ያነሰ ገቢ እያገኘ ኑሮውን ይገፋል።

በቀጠናው የሚንቀሳቀሰው ኤም 23 የሚባለው ሽብርተኛ ቡድን ደግሞ ለሀገሪቱ የበለጠ ፈና እየሆነ ይገኛል። ቡድኑ ዜጎቿን ለሞት ሀብቷን ደግሞ ለብክነት አሳልፎ እየሰጠባት እንደሚገኝ ይታወቃል።

በዚህ ሁሉ መሀል የተደረገው የፖፕ ፍራንሲስ ጉብኝት በኮንጎ ብቻም የሚያበቃ አይደለም ሌላኛዋ ሰላም የራቃት ጎረቤታችንን ደቡብ ሱዳንንም የሚጨምር ነው።

በዚያም ጳጳሱ ስለሰላም ይሰብካሉ ስለአንድነትም ይናገራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ይህ የፖፕ ፍራንሲስ ጉዞ ወደ መንበረ ጵጵስናው ከመጡ የጎበኟቸውን ሀገራት 60 ያደርሳቸዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-02-01