ሀገሬ ቲቪ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሞቃዲሾ ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምሥራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጠናዊ መድረክ ለመሳተፍ ሞቃዲሾ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ እና ኬኒያ የመከላከያ ሚኒስትሮች በምስራቅ አፍሪካ ሽብርተኝነት መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች በሶማሊያ ርእሰ መዲና ሞቃድሾ ሲመክሩ ሰንብተዋል፡፡

የሀገሪቱ የመረጃ ሚኒስትር ሶማሊያ በአራቱም አቀጣጫዎች ከአልሻባብ ጋር ጦርነት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የሽብር ስጋት ለመቀንስ የሶማሊያ ጦር ከአጎራባች አገራት መከላከያ ሰራዊት ጋር በትብብር መስራት በሚችሉባችው ጉዳዮች ላይም ምክክር ተድርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ከሶማሊያው አቻቸው እንዲሁም ከአፍሪካ ሰላም ማስከበር ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ተነጋግረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-02-01