ሀገሬ ቲቪ

15 የውጪ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በሱማሌ ክልል በስራ ላይ በነበሩ 15 የውጪ መገናኛ ብዙሃንን ማገዱ ተሰማ።

ባለስልጣኑ የስራ ገደብ የጣለባቸው ከፌደራል መንግሥት የሚዲያ ተቆጣጣሪ አካል ፈቃድ ሳይኖራቸው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ላይ ነው ተብሏል ።

ተቋማቱ ተገቢውን የሚዲያ እውቅና ባለማግኘታቸው ከስራ እንደታገዱ ቢነገርም የክልሉ ጋዜጠኞች ማኅበር ግን እርምጃው የተወሰደው በክልሉ እያጋጠመ ያለውን ሙስናና ከፍተኛ ድርቅ የሚያጋልጡ መገናኛ ብዙሃኖች ላይ ነው ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ከስራ ያገዳቸውን ተቋማት ዝርዝር ይፋ አላደረገም።

በዮሴፍ ከበደ
2023-02-01