ሀገሬ ቲቪ

የነጃጅ ዋጋ መናርን መቆጣጠር አልተቻለም

የፔትሮሊየም ላኪ ሀገሮች ድርጅት (ኦፔክ) የነዳጅ ዋጋን መቆጣጠር እንዳልቻለ ተገለፀ።

ከየሃገራቱ የተውጣጡ ሚኒስትሮች በጉዳዩ ዙሪያ በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።

የወቅቱ የዓለም የፔትሮሊየም ላኪ ሃገራት ድርጅት ፕሬዝዳንት ገብርኤል ምባጋ በየጊዜው በገበያው ላይ አለመረጋጋት እየታየ ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የሩሲያ እና የዩኩሬን ጦርነት በነዳጅ ገበያው ላይ የፈጠረው ችግር ነው ተብሏል። ከሰሞኑ አንድ በርሚል ነዳጅ ዘጠና ዶላር ገደማ እየተሸጠ ይገኛል።

በማህሌት አማረ
2023-02-01