ሀገሬ ቲቪ

ፍልስጤም ለውጥረቱ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች

የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አባስ በቀጠናው ለተፈጠረው ውጥረት እስራኤል ተጠያቂ ናት አሉ።

በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ፍልስጤም ዌስት ባንክ ደርሰዋል።

መሀሙድ አባስ ከብሊንከን ጋር በነበራቸው ቆይታ እስራኤል በፍልስጤም ምድር ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ተጠያቂ ናት ማለታቸው ተሰምቷል።

አባስ እስራኤል በፍልስጤም ምድር ያደረገችውን ወረራ እና የሰፈራ ፖሊሲ ልታስቆሟት አልቻላችሁም ሲሉም የዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ ኮንነዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-02-01