ሰዎች በተፈጥሮ ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለአይነ ስውርነት ይዳረጋሉ። ታዲያ እነዚህን ለአይነ ስውራንን ለማገዝ የተለያዩ ነገሮች ሲደረጉ ይስተዋላሉ። ከወደ ጃፓን አንድ አይነ ስውር ሳይንቲስት ማየት ለተሳናቸው ሰዎች የሚያግዝ ስማርት ሻንጣን ሰርታለች፡፡
ይሄ ስማርት ሻንጣ አይነ ስውር የሆኑ ሰዎች ልብሶቻቸውን ወይንም የሚጠቀሙባቸውን ቁሶች በቀላሉ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ሳይሆን መንገድ እንዲመራቸው መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል።
ይሄ ሻንጣ ብዙ ጊዜ አይነ ስውራን የሚጠቀሙበትን ነጭ ዘንግ አልያም በውሾች ሳይታገዙ በዙሪያቸው ያለውን አቅጣጫ ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚመራቸው መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
ይሄንን አዲስ እና ዘመናዊ የሚባለውን አቅጣጫ ጠቋሚ ሻንጣ አይነ ስውራን ከስልካቸው ጋር አገናኝተው የት እንደሚሄዱ በማባስገባት በቀላሉ ወደ ሚፈልጉበት መድረስ እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
ስማርት ሻንጣው ሴን ሰር፣ ካሜራ እና ጂፒኤስ ስርዓት የተገጠመለት ነው። ይህም ደግሞ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ጋር እንዳይጋጭ፣ ሌሎች ጉዳት የሚያስከትሉ ነገሮች እንዳያጋጥመው አስር ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለተጠቃሚው በሻንጣው እጀታ ውስጥ ባሉት ሃፕቲክ ሴንሰሮች አማካኝነት መልዕክት ያስተላልፋል።
ይሄም በቤት ውስጥም ይሁን ከቤት ውጭ ለሚኖራችው እንቅስቃሴ አመቺ ነው ተብሏል።
ይሄንን ስማርት ሻንጣ ሃሳቡን አምጥታ እውን እንዲሆን ያደረገችው የ65 አመቷ ቺኮ አሳካዋ በአስራ አራት አመቷ ያጋጠባት ድንገተኛ አደጋ የአይን ብርሃኗን ሙሉ ለሙሉ ያጣችው እንስት ናት፡፡
አሳካዋ ለበርካታ አመታት በተጨናነቁ ጎዳናዎች ስትዘዋወር ያጋጠሟት ችግሮች በ ፈረንጆቹ 2017 ይሄንን የመፍተሄ ሃሳብ እንዳመጣ አግዞኛል ብላለች፡፡
በአሁኑ ጊዜ ይህ የረቀቀ መሣሪያ እስከ የካቲት 6 ድረስ በሚራይካን ሙዚየም ፊት ለፊት ያለበት ሰው ሙከራ ሊያደርግበት ይችላል ተብሏ ።
ይሄንን የቴክኖሎጂ ሃሳቧን በገንዝብ ሲደግፏት የነበሩት አይ ቢ ኤም፣ ኦምሮን፣ አልፕስ አልፓይን የተሰኙት የጃፓን ድርጅቶች በቀጣይ በኤርቶርቶች፣ በገበያ ማዕከላት እና በባቡር ጣቢያዎች አካባቢ ወደፊት ምርቶቹ ለሽያጭ የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
በማህሌት አማረ
2023-02-01
