ሀገሬ ቲቪ

ቤተክርስቲያኗ የመንግስትን መግለጫ ተቃወመች

ቤተክርስቲያኗ መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት፤ ህገወጥ ናቸው ስትል የፈረጀቻቸው አካላት እየፈፀሙት ነው ላለችው ህገወጥ ድርጊት እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትላንትናው ዕለት መንግሥት ቤተክርስቲያኗን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ እንደማትቀበለው ገልጻለች።

መንግስት በመግለጫው በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ እና ጭካኔ የተሞላበትን የአደባባይ ግድያ እና የህዝብ ፍጅትን ያልጠቀሰ ብሎም ሐዘኑንም እንኳን ያልገለፀ መሆኑ የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል ብላለች።

ቤተክርስቲያኗ መንግሥት ለሕገ ወጥ አካላት ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልዕልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እናሳስባለን ብላለች።

በብሩክ ያሬድ
2023-02-06