ሀገሬ ቲቪ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ለሕዝበ ውሣኔ መራጮች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል።

ድምጽ የመስጠት ሂደቱ በክልሉ ስድስት ዞኖች ማለትም በኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ በጋሞ ፣ ጌዴኦ እና ጎፋ እንዲሁም በአምስት ልዩ ወረዳዎች ፤ በቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ እና ዲራሼ ላይ ሲደረግ መዋሉን ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

ቦርዱ በዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች የተለያዩ የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት አጋጥመውት እንደነበር ያሳታወቀ ሲሆን በትብብር እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ተሞክሯል ብሏል።

በወላይታ ዞን ሶርቶ ቀበሌ ሶርቶ 1፣ በይርጋ ጨፌ ማስተባበሪያ ማእከል ስር በሚገኘው አዳሜ ምርጫ ጣቢያ ሱኬ፣ በጋሞ ሰላም በር በዶሞኦ ቀበሌ በዶሞኦ ምርጫ ጣቢያ ወማለ 1 የምርጫ የህግ ጥሰቶች አጋጥመውት እንደነበርም አስታውቋል።

በአብርሃም በለጠ
2023-02-06