ኢትዮ ቴሌኮም ለ250 የቢዝነስ ጀማሪ ተቋማት ዕድል የሚሰጥ "ኢትዮቴል ኢኖቬዥን" የተሰኘ አዲስ ፕሮግራም ይፋ አደረገ።
ፕሮግራሙ ከሁአዌ ኩባንያ ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን በሀገራችን ልጆች ተሰርተው በፋይናንስ እጥረት የቆሙ ፈጠራዎችን የሚያግዝ ነው ተብሏል ።
ኢትዮቴሌኮም የፍይናንስ ፣የሥልጠና፣ የቁስ፣ የሌሎች ሀገራት ልምድ ማጋራት እና ሌሎች ድጋፎችን ለጀማሪ የሥራ ፈጣሪዎች አደርጋለሁ ብሏል።
ፕሮግራሙ በ 3 ምዕራፎች ተከፍሎ በመጀመሪያና በሁለትኛ ምዕራፍ 250 ሰወችን ተጠቃሚ ሲያደርግ ሶስተኛው ምዕራፍ ወደ ምርምር ስራ የሚያሸጋግር መሆኑን የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-02-06
