ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግስታት ኃላፊ ከማሊ ተባረሩ

ማሊ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ተወካይን ከሀገሯ አባረረች።

ማሊ ኃላፊው የሲቪል ማህበረሰቦችን ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በምስክርነት በመምረጣቸው ነው በ48 ሰዓት ውስጥ ከሀገሬ ውጡ ያለቻቸው።

በማሊ ደረሱ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት በዚያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ተቋም የተፈፀሙትን በደሎች ለማስረዳት አድሏዊ የሆነ እና ያልተገባ ምስክሮችን ተጠቅሟል ስትም ከሳለች።

ድርጅቱ ለፈፀመው አድሏዊ ተግባር ብጠይቅም ምላሽ አላገኘሁም ነው ያለችው።

በሳምሶን ገድሉ
2023-02-06