በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ለሊሴ ነሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በእቅድ ወራቱ 203 ባለሀብቶች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ ታቅዶ 118 ባለሀብቶች መሰማራታቸውን ገልፀዋል። ኮሚሽነሯ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደውጪ ከሚላኩ ምርቶች 223 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 156 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል ያሉ ሲሆን ። ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 21 በመቶ እድገት ወይም የ27 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን አመልክተዋል ። ኮሚሽነሯ የተገኘው ገቢ ከአምናው የተሻለ ቢሆንም ከ ታቀደው ገቢ አንፃር ዝቅ ያለው የኢትዮጵያ ከአገዋ መሰረዝ : የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም የሩሲያና ዩክሬን ቀውስ የፈጠረው ጫና ነው ብለዋል። ጨምረውም እነዚህን ጫናዎች ለመቅረፍ የተለያዩ የ ኢሮፕ ገበያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በዘጠኝ ወራቱ 114 ድርጅቶች ወደማምረት እዲሸጋገሩ ታቅዶ 117 ድርጅቶች ወደስራ የገቡ ሲሆን ይህም የእቅዱን መቶ በመቶ ማሳካታቸውን ኮሚሽነሯ ገልፀዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-05-10
