በኢንዲኔዥያ የሚገኙ የኔ ቢጤዎች በቲክቶክ መለመን ጀምረዋል። ይህም የሆነው ሃገሪቱ አንድም ሰው መንገድ ላይ ተቀምጦ መለመን አይችልም በማለቱ አነው ተብሏል።
ዘመናዊ ናቸው የትባሉት ለማኞች ደግሞ በእድሜያቸው የገፉ እናቶች መሆናቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
በቲክቶክ መለመን የጀመሩት ኢንዶኔዥያዪያን መነጋገሪያ ሁነዋል። አብራችሁን ከቆያችሁ ወደ ኋላ ላይ እናጫውታችኋልን።
በኢንዲኔዥያ የሚገኙ የኔ ቢጤቆች በቲክቶክ መለመን ጀምረዋል። ይህም የሆነው ሃገሪቱ አንድም ሰው መንገድ ላይ ተቀምጦ መለመን አይቻልም በማለቷ ነው ተብሏል። ዘመናዊ ናቸው የትባሉት ለማኞች ደግሞ በእድሜያቸው የገፉ እናቶች መሆናቸው የብዙዎችን ቅልብ ስቧል።
ኢትዮጲያን ጨምሮ የአለምን ሃገራት አንድ የሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል በመንገድ ላይ ተቀምጠው የሚለምኑ ሰዎች መኖራቸው ነው። ከወደ ኢንዶኔዥይዝ የተሰማው ደግሞ የጎዳና ላይ ልመናን ለማጥፋት የዘየደችው መላ የኔቢጤዎቹ ዘመናዊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ተብሏል።
ከ90 ሚሊየን በላይ ቲክቶክ ተጠቃሚ ኢንዶኔዢያዊያን እንደ መልካም እድል የተጠቀሙት የኔቢጤዎች ደግሞ የሃገሪቱ መንግስት የጣለባቸው እገዳ በኑሯችን ላይ ተፅዕኖ አላሳደረብንም ብለዋል።
በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የነገሱት እነዚህ የኔቢጤዎች ደግሞ በእድሜ የገፉ እናቶች መሆናቸው የበለጠ ቀልብ እንዲስቡ አድርጓቸዋል።
እነዚህ በእድሜ የገፉ እናቶች ኑሯቸው ምን እንደሚመስል ፈጠራ በታከለበት ትዕይንት በማጀብ እያሳዩ ይገኛሉ። የጭቃ መታጠቢያ ብለው በሰየሙት የምስል ደግሞ ብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነው።
ቲክቶክን የገንዘብ ማግኛ ያደረጉት እነዚህ እናቶች እራሳቸው ላይ የቆሸሹ ውሃዎችን በመድፋት ለረጅም ሰአት በቲክቶክ በቀጥታ በመታየት ከሃብታሞች በድጋፍ መልክ የሚሰጧችወን ስጦታ ወደ ጥሬ ገንዘብ በመቀየር ኑሮዋቸውን በመግፋት ላይ ናቸው።
ኢንዲኔዚያ ብዛት ያላቸው የቲክቶክ ተጠቃሚዎ ያሏት የአለም ሁለተኛዋ ሃገር ናት። ይሄንን እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሙት እነዚህ ጥበበኛ የኢንዶኔዥያ የኔቢጤዎች ከልመና ባሻገር ያላቸውን የፈጠራ ተሰጦ ለችግራቸው መፍቻ በማድረጋቸው የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።
አንድ በዚሁ የማህበራዊ ገፅ ልምና ላይ የተሰማሩ እናት ልብሳቸውን እንደለበሱ በጎረቤታቸው በሱልጣን አኪያር የቲክቶክ አካውንት የተለቀቀው ምስል ብዙዎች የተጋሩት ነበር።
ይሄንንም ምስል የሃገሪቱ የመረጃ እና የህዝብ ግንኙነት ሚኒስቴር ጥያቄ መሰረት ከገፁ እንዲጠፋ ተደርጓል። ቢዚህም የኢንዲኔዢያ መንግስት በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወሩ ሌሎች የልመና ምስሎችንም ሊያግድ ይችላል ተብሏል።
በማህሌት አማረ
2023-02-06
