ከትላንት በስቲያ በቱርክ እና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ዓለምን ሁሉ ያስደነገጠ ነበር።
አደጋውን የከፋ ያደረገው ደግሞ ከመጀመሪያው ርዕደ መሬ በኋላ የተረፉትን ለማዳን ጥረት እየተደረገ ባለበት ግዜ ሌላ ከፍተኛ ርዕደ መሬት መከሰቱ ነው።
ታዲያ በዚህ ሁሉ መሀል ዓለም አንድ ተንቀሳቃሽ ምስልን ተመለከተ።
አንድ ጨቅላ ገና ይህቺን አስከፊ ዓለም ወዳጅ ዘመድ ደስታ ሳይሆን ሰዎችን ለማዳን በሚደረግ ርብርብ ጫጫታውስጥ ድምፁን አሰማ።
ካሃል አል ሰውሃዲ አጋጣሚውን እንዲህ ያስታውሰዋል።
አንድ ቤተሰብ ሙሉ ሞቶ እሬሳቸውን በአንድ ቦታ ላይ አገኘን፤ ፍርስራሹን ለማንሳት ስንቦረቡር ድምፅ ሰማን። ሟች ቤተሰቦችን ስናገኛቸው ድምጽ የሚባል አልነበረም ግን ወደ ታች ፍርስራሹን እየቆፈር ስንሄድ ድምፁን ሰማን። ቆፍረን ፍርስራሹን ስናነሳ ጨቅላውን አገኘን። ጨቅላው እትብቱ እንኳን አልተቆረጠም፤ እናትየው ሞታለች፤ እትብቱን ቆርጠን ወደ ሆስፒታል ወሰድናት።
እናት፣ አባት፣ እህት እና ወንድሞቿ እሷ በተወለደችበት ዕለት ይህቺን ዓለም በአሰቃቂ ሁኔታ የተሰናበቱባት ጨቅላ አሁን በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላት ትገኛለች።
በአደጋው ሰዓት ለበርካታ ህመሞች መጋለጧን የተናገሩት ሀኪሞች አሁን ኝ በመልካም ጤንነት ላይ ነች ብለናል።
ሌላኛው አንጀትን የሚያንሰፈስፍ ኔና ደግሞ ይህኛው ነው።
በርዕደ መሬቱ ክፉኛ በተጎዳችው ቱርክ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ይዞት የወጣው ፎቶ ነው።
ይህ አባት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች እስኪ መጡ ድረስ አይደለም እዚህ ጋር ሆኖ እየተበቀ ያለው፤ በፍርስራሹ ስር ያለችዋንም ልጅ ተስፋ እየሰተ እያቆያትም አይደለም፤ ይህ ሕንፃ የተናደባት በላይዋ ተጭኖ ህይወቷን የነጠቃት የ15 ዓመት ልጁን እጅ የያዘ አባት ፎቶ ነው።
ገና ቦርቃ ያልጠገበች የአይኑን ማረፊያ በእንዲህ ያለ ዘኛኝ ሁኔታ ያጣ አባት ነው።
ዓለም እንዲህ ናት በሰኮንዶች ልዩነት ውስጥ አሉ ያልናቸውን የተመካንባቸውን ነገሮች ሁሉ እንዲህ ባለ ሁኔታውስጥ እናጣቸዋለን።
ሁሉም ወደ ነገርነት ይለወታል፤ ታዲያ ለምን እንከፋለን? ምን ፈልገን? በያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ይመለስ።
በሳምሶን ገድሉ
2023-02-08
