ባለፉት 8 ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት 787 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተናገረ።
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የገበያ መዳረሻዎቿን በማስፋት በሰራችው ስራ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ወደ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ ቻይና እና አውስትራሊያን ጨምሮ ወደ አዳዲስ መዳረሻዎች የቡና ምርቷን በስፋት መላክ ጀምራለችም ተብሏል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-03-18
