የዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት (ILO) በሳምንት አስፈላጊ የስራ መስኮች ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በቂ ደመወዝ እንደማይከፈላቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርጃን ዋቢ አድርጎ አስታውቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ የጤና ባለሙያዎች እንደሚኙበት ድርጅቱ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡
የዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት (IOL) በዚህ ሳምንት ባወጣው ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አገራት የሰራተኞቻቸውን የስራ ከባቢ እና ደሞዝ እንዲያሻሽሉ ጠይቋል፡፡
ተቋሙ ባወጣው ጥናት ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ አገራት 29 በመቶ ሠራተኞች ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አስታውቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ የጤና ባላሞያዎች፣ የምግብ ዝግጅት ባለሞያዎች፣ የመልዕክት አድራሽ እና የጥበቃ ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡
ጥናቱ 90 አገራት ላይ መሰረት አድርጎ የተሰራ ሲሆን ኬንያ ዝቅተኛ ደሞዝ ከፋይ በመሆን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች፡፡
በኬንያ ከ50 በመቶ በላይ ሰራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል፡፡
በይስሐቅ አበበ
2023-03-21
