ሀገሬ ቲቪ

የፒ ኤስ ቪ አይንዶሆቨን ለ40 ዓመታት ወደ ስታዲየም ድርሽ እንዳይል ታገደ

የፒ ኤስ ቪ አይንዶሆቨን ለ40 ዓመታት ወደ ስታዲየም ድርሽ እንዳይል ታገደ፡፡

ፒ ኤስ ቪ አይንዶሆቨን በአውሮፓ ሊግ ከሲቪያ ጋር የመልስ ጨዋታውን ሲያደርግ ወደ ሜዳ ዘሎ የገባውን ደጋፊውን ለአራት አስርት ዓመታት ወደ ስታዲየም እንዳይገባ አግዶታል።

ፒ ኤስ ቪ አይንዶሆቨን ደጋፊው የሲቪያውን ግብ ጠባቂ ማርኮ ድሚትሮቪች ፊቱን በጥፊ በመምታት ንዴቱን ለማቀዝቀዝ ቢሞክርም የሲቪያው ግብ ጠባቂ ማርኮ ድሚትሮቪች ከመሬት ጋር አጣብቆ አላንቀሳቅስ ብሎት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ለአንድ ወር ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው ፒ ኤስ ቪ አይንዶሆቨን ደጋፊውን እስከ 2063 ወደ ስታዲየም እንዳይገባ ወስኗል።


2023-03-22