ሀገሬ ቲቪ

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግሥት የተበረከተላቸውን የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተረከቡ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግሥት የተበረከተላቸውን የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተረከቡ።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ሽልማታቸውን በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ሚስተር ሺባታ ሂሮኖሪ እጅ ተረክበዋል።

በጃፓንና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርት ዲፕሎማሲና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ፣ በሌሎች ሀገራትና አካባቢዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ፣ ለአትሌቲክስ እድገት፣ ለአገር ሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና አግኝተዋል።

ይህ እውቅናና ሽልማት እ.ኤ.አ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግሥት የሚሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ መረጃ ያመለክታል።

በይገደብ ዓባይ
2024-04-03