አሐዱ ባንክ ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማቱን አስታውቋል፡፡
የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰፊዓለም ሊበን ባንኩ ደንበኞቹ የሚያቀርቡትን የተለያዩ የውክልና ሰነዶች በኦንላይን ማረጋገጥ የሚቻልበትን አማራጭ ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡
አቶ ሰፊዓለም የተቋማቱ ቴክኒካል ቡድኖች ሰነዶችን በዲጂታል አማራጭ ማረጋገጥ የሚያስችለውን አሰራር ተግባራዊነት አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡
መረጃዎቻችንን፦
Facebook: https://www.facebook.com/hagerietv
Twitter: https://twitter.com/HagerieT
Instagram: https://www.instagram.com/hagerie_tel...
Telegram: https://t.me/Hagerie_TeleVision
YouTube: https://www.youtube.com/hagerietv
Website: https://www.hagerietv.com
በአብርሃም በለጠ
2023-03-22
