መንግሥት በግማሽ ዓመት 100 ቢሊዮን ብር ያህል ቀጥታ ብድር መውሰዱ ተሰምቷል፡፡
መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) በ2015 በጀት ዓመት ሁለተኛው ሩብ ዓመት 40 ቢሊዮን ብር በቀጥታ ብድር የወሰደ ሲሆን፣ ይህም በመጀመርያው የሩብ ዓመት ከወሰደው 60 ቢሊዮን ብር ጋር በስድስት ወራት ውስጥ 100 ቢሊዮን ብር ቀጥታ ብድር መውሰዱን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
መንግሥት በ2014 ዓ.ም. ሙሉ በጀት ዓመት የወሰደው የተጣራ ቀጥተኛ ብድር 76 ቢሊዮን ብር እንደነበርም ዘገባው አስታውሶ ብሔራዊ ባንክ ዘንድሮ ለመንግሥት የሰጠው ቀጥታ ብድር ከከዚህ ቀደሙ ጊዜ ከሰጠው ትልቁ መሆኑን ፅፏል።
በ
2023-03-22
