ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾመዋል።
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሃት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማቆም በፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም በማስፈለጉ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመጋቢት 9 ቀን 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን አፅድቋል።
በዚሁ ደንብ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾመዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈፃሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-03-23
