ሀገሬ ቲቪ

ግብፅ ከህዳሴው ግድብ ድርድር እራሷን ልታስወጣ ነው

ግብፅ ከህዳሴው ግድብ ድርድር እራሷን ልታስወጣ ነው፡፡

ግብፅ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ከሚመራው ቴክኒካዊ የህዳሴው ግድብ ድርድር እራስዋን ልታስወጣ መሆኑ ተሰምቷል።

የግብፅ ባለስልጣናት ነገሩኝ ሲል ዘ ኒው አረብ የተሰኘ ድረ ገፅ እንዳስነበበው ባለሥልጣናቱ ውይይቱ ለውጥ እያመጣ አይደለም የሚል ቅሬታ አላቸው።

ግብፅ የህዳሴው ግድብ ወደ ተግባር ሲገባ በኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ ባለሙያዎቿ ቀጥተኛ ወሳኝ አካል አድርጋ ማስቀመጥን ትሻለች።

በአፍሪካ ሕብረት የሚመራው የግድቡ ድርድር ግብፅ ታሪካዊ የውሃ መብት አለኝ እሱ ሊነካብኝ አይገባም በሚል በተደጋጋሚ መከራከሪያዎችን ስታነሳ ሰንብታለች።

ይህም በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ለውጥ ሳይመጣ ባለመስማማት እንዲለያዩ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-01-24