የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ‘’በጌምድር’’ የተሰኘ የቤተመዛግብት ማዕከል አቋቁሞ አስመረቀ።
ማዕከሉ የተለያዩ የፅሁፍ ቅርሶችን እና መዝገቦችን ሰንዶ የያዘ እንደሆነ በዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር አቶ መሰረት ወርቁ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በጌምድር ጥንታዊ እና ታሪካዊ ስም ስለሆነ ለማዕከሉ መጠሪያነት እንደተመረጠም አስረድተዋል።
በማዕከሉ የተለያዩ ታሪካዊ መዛግብት፣ የፅሁፍ ቅርሶች እና ፎቶዎች ይገኛሉ።
የተለያዩ ጥናቶች እና ምርምሮችን ለማድረግ የቤተመዛግብት ማዕከሉ ይረዳል ተብሏል፡፡
መዛግብቱ እና ተያያዥ ቅርሶቹ መቀመጥ በሚገባቸው ጥንቃቄ እና ቴክኖሎጂ የተቀመጡ ባለመሆናቸው ሁላችንም ትልቅ የቤት ሥራ ይጠበቅብናልም ሲሉ አቶ መሰረት ተናግረዋል፡፡
በሙሉጌታ በላይ
2023-03-27
