
የኬንያ አየር መንገድ እና የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ በመጪው የፈረንጆቹ 2024 በጋራ መስራት እንደሚጀምሩ አስታወቁ።
ሁለቱ አየር መንገዶች በመንገደኞች፣ በጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለተጠቃሚዎች ተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን እና ተደራሽ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።
የሁለቱ ሀገራት አየር መንገዶች ከ3 ዓመት በፊት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት የመጀመሪያውን የትብብር ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ተፈራርመው እንደነበር ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2023-03-27