ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየተጠቀሙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየተጠቀሙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡

ፓርቲው ከተማ እና መሰረተ ልማት ትይዩ ሚኒስቴር ከተማ ፕሮጀክቶች ሙያዊ ትንተና ማድረጉን አስታውቋል።

በከተማዋ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ከህጋዊ የግዢ መመሪያ ውጪ በልዩ ትኩረት በተለይ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የቅደም ተከተል መርህን ያላገናዘቡ መሆናቸውን ያነሳው ኢዜማ ሀገራዊ ምርትን ከማበረታታት ይልቅ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየተጠቀሙ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡

አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ያሉት በውጭ ድርጅቶች በመሆኑ የእውቀትም ሆነ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥቅም የማያስገኙ መሆናቸውን መገምገሙን አስታውቋል፡፡

በ ይስሐቅ አበበ
2023-03-27