ሀገሬ ቲቪ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ልዑላዊነት ዋና ስጋት ምንጭ ሆኖ የምናየው አብይ የሚመሩት መንግስት መሆኑን በመጠቀስ አፋቸው ኢትዮጵያ አትፈርስም ቢሉም በተግባር ግን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በመንግስታቸው እየተናዱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም የበርካታ ሀገራት መሪዎች መሰል ኃላፊነትን በወጉ አለመወጣት ጉድለት ሲያሳዩ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀው ስልጣናቸውን ሲለቁ ይታያል፤ በሀገራችንም የቀድሞ ጠ/ሚ ክቡር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ህዝባዊ ተጠየቅነት ሲቀርብባቸው ስልጣን መልቀቃቸውን እናስታውሳለን እርስዎም ወደ ስልጣን የመጡት በዚሁ ተጠየቅ ምክንያት ነው፤ እርስዎስ ስልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት? ሲሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ጠይቀዋል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-03-27