ሀገሬ ቲቪ

በዚህ በ 2 ወይም 3 ወራት ዉስጥ የተከሰተዉ የዋጋ ንረት እንደሚባለዉ የከፋ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

በዚህ በ 2 ወይም 3 ወራት ዉስጥ የተከሰተዉ የዋጋ ንረት እንደሚባለዉ የከፋ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፉት 5 ዓመታት ዉስጥ እኛ የወሰድነዉ አንድ ዶላር ኮሜርሻል ብድር የለም እንደውም ከነበረብን ብድር ላይ 1.7 ቢሊየን ዶላር ከፍለናል ብለዋል፡፡

አክለውም በዚህ በ 2 ወይም 3 ወራት ዉስጥ የተከሰተዉ የዋጋ ንረት እንደሚባለዉ የከፋ አይደለም፣ አቅርቦቱን በመጨመር እና ሁኔታዎችን በማሻሻል የሚረጋጋ እንደሚሆን ተስፋ አለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በማህሌት አማረ
2023-03-27