መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ መረጃዎች በማዘመን ሁሉም አርሶአደር እኩል መረጃ እንዲኖረው ለማድረግ ብሄራዊ ዲጅታል የግብርና ኤክስቴንሽን እና ምክር አገልግሎት ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቷል።
የብሄራዊ ዲጅታል የግብርና ኤክስቴንሽን እና ምክር አገልግሎት ፍኖተ-ካርታ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ የተደረገ ሲሆን መድረኩ የተዘጋጀው ግብርና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በመቀናጀት ነው፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መለሰ መኮንን መንግሥት ስለግብርና መረጃዎችን ዲጂታይዝድ በማድረግ ሁሉም አርሶአደር እኩል መረጃ እንዲኖረው በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ እያዘመነው ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጀነራል ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ የብሄራዊ ዲጅታል የግብርና ኤክስቴንሽን እና ምክር አገልግሎት ፍኖተ-ካርታ አላማው የአርሶ አደሩን ምርታማነት መጨመር፣ ሴት እና ወጣት አርሶ አደሮችን ማብቃት እንዲሁም ምግብና ስርዓተ- ምግብን ማሻሻል እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-03-27
