የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በትኩሱ ለውጭ ገበያ የሚያደርሱ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ እና በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ መዳረሻቸው እንዲጓጓዙ ለማድረግ የገዛቸው ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮች በመጪው ሳምንት መጨረሻ ጅቡቲ ይደርሳሉ ብሏል።
ከቻይና የተገዙት እነዚህ ኮንቴይነሮች በጅግጅጋ መርከብ ተጭነው ወደ ጅቡቲ እየመጡ ሰሆን ለእነዚህ ባለማቀዝቀዣ ኮንቴይነሮች ማስተናገጃነት በሞጆ ወደብ ልዩ ተርሚናል መዘጋጀቱንም ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-03-28
