ሀገሬ ቲቪ

በተያዘው የፆም ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት ገለፀ።

በተያዘው የፆም ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት ገለፀ።

የለጋሾች ቁጥር በመቀነሱ ምክንያት ተቋሙ በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ገልፀዋል፡፡

ከአጿማት ዓላማ አንፃር ህይወትን ማትረፍ ፋይዳው ትልቅ ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከፆም ሰዓታት በኋላ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአብርሃም በለጠ
2023-03-29