
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ዜጎች ለህግ ተገዥ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት በአገሪቱ የተፈጠረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነው፡፡ የዊልያም ሩቶ ታቀናቃኝ የሆኑት ራኤላ ኦዲንጋ ሰኞ እና ማክሰኞ ተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ፖለቲካል ውይይቶች እንዲደረጉ ጠይቀዋል፡፡ በጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ሩቶ በአገሪቱ የታየው የህግ ጥሰት ያለቅጣት በቸልታ እንደማይታለፍና ሁሉም ኬንያውያን ለህግ የበላይነት መገዛት አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በወንድማገኝ አበበ
2023-03-29