ፈረንሳይ እና ስዊዘርላንድ በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ክስ ሊመሰረትባቸው ነው፡፡
ሀገራቱ ክስ የሚመሰረትባቸው የአካባቢ አየርን በመጠበቅ ለዜጎቻቸው ጤናማ እና ምቹ እንዲኖር ባለማድረጋቸው ነው ተብሏል፡፡
በስዊዘርላንድ ራሳቸውን የአየር ንብረት አዛውንቶች ክለብ ብለው የሰየመው አረጋውያን አገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገችው ያለው ጥረት አነስተኛ ነው በማለት ነው ለአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያስገቡት፡፡
በፈረንሳይ የቀድሞ የግራንዴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ዴሚየን ካርሜ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በቂ እርምጃዎችን አልወሰድችም የሚል ክስ ማስጋባታቸው ተሰምቷል፡፡
በብሩክ ያሬድ
2023-03-29
