ኢትዮጵያ እና እስራኤል በብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ላይ በጋር ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
እየሩሳሌም የህዝብ ግንኙነት ማዕከል እና የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የውጭ ፖሊሲ ጥናት የውሃ እና የምግብ ዋስትናን ጨምሮ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ማድረግ ያለብን የመጀመሪያው ነገር የምግብ ዋስትናን ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስክ ወደ ብሄራዊ ደህንነት መስክ ማሸጋገር ነው ሲሉ የጄሲፒኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዬቺኤል ኤም ተናግረዋል፡፡
የጄሲፒኤው ፕሬዝዳንት ዳን ዲከር በበኩላቸው የእስራኤልን የቴክኖሎጂ ሃይል ከኢትዮጵያ ሀብት ጋር ማጣመር ከተቻለ ሀገሪቱ ወደ አለም አቀፍ የዲፕሎማሲያዊ ሀይል ማደግ ትችላለች ብለዋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-03-31
