ሀገሬ ቲቪ

ግብፅ የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ የምታደርገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ኢትዮጵያ ገለፀች፡፡

ግብፅ የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ የምታደርገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ኢትዮጵያ ገለፀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳለው ጉዳዩ የ 11 ተፋሰስ ሀገራት እንጂ የሌሎች ሊሆን አይገባውም። ሰላማዊ የልማት ፕሮጀክትን የዓለም አቀፍ የቀውስ ምንጭ አድርጎ ለመቁጠር የሚደረገው ጥረትም ውጤት እያመጣ ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ እንዳለው ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ፣ ለሱዳንና ለግብፅ የትብብር እንጂ የጠብ ምንጭ የሚሆንበት አንዳች ምክንያት የለውም ብሏል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ ከቀናት በኋላ 12 ዓመት የሚሆነው ሲሆን ግንባታውም 90 በመቶ ደርሷል፤ አሁን ላይ በተወስኑ ዩኒቶቹም ኃይል እያመነጨ ነው።

በብሩክ
2023-03-31