
የምፃትን ቀን በመፍራት ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ዩጋንዳውያን በኢትዮጵያ እየኖሩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለፀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ መለስ አለም ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ከምስራቅ ዩጋንዳ የመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዩጋንዳውያን በደቡብ ክልል ያንጋቶም ኑሮ መጀመራቸውን ገልፀዋል።
የአንድ ቤተክርስቲያን አማኞች ናቸው የተባሉት እነዚህ ዩጋንዳውያን ቆይታ በተመለከት መንግሥት ምን እንደወሰነ ያሉት ነገር የለም።
የዩጋንዳ መንግሥት ግን ጉዳዩን እየመረመረ እንደሆነ እና የምፅአትን ቀን ፈርተው ወደ ኢትዮጵያ የሄዱትን ዜጎቹን ጉዳይ በቅርበት እንደሚከታተልም አስታውቋል።
በብሩክ ያሬድ
2023-03-31