ሀገሬ ቲቪ

ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት እንደሚጀመር ተጠቆመ፡፡

ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት እንደሚጀመር ተጠቆመ፡፡

ዛሬ በመዲናዋ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚሆን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር (ዶ/ር) አለሙ ስሜ ተናግረዋል።

ግብይቱ በዲጂታል መንገድ መከናወኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

በቅርቡም የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር ተነግሯል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-03-31