ሀገሬ ቲቪ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት ዕቅድ የተገነቡ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች እና ለልማት ተነሺዎች አስረከቡ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት ዕቅድ የተገነቡ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች እና ለልማት ተነሺዎች አስረከቡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ በክፍለ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስተባበር በስድስት ብሎኮች የተገነቡ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፣ ለውስብስብ የጤና እክል የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ እና በከተማው እየተከናወነ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት ለተነሱ ነዋሪዎች አስረከቡ።

ዛሬ የቤት ባለቤት ከሆኑት ውስጥ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ይገኙበታል።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ተለይተው በዛሬው ዕለት የቤት ቁልፍ ለተቀበሉ ነዋሪዎች ከንቲባ አዳነች የማዕድ ማጋራትንም አድርገዋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-01