ሀገሬ ቲቪ

ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል።

ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል።

ከዚህ ቀደም ከነበረው በበርሜል ከ5 ዶላር ወይም ከ7 በመቶ በላይ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል፡፡

ጭማሪው የተከሰተው ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን ከ1 ሚሊዮን በርሜል በላይ ከምርታቸው ላይ እየቀነሱ መሆናቸውን ተከትሎ ነው።

ሩሲያ ዩክሬይንን በወረረችበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሶ ነበር።

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-03