አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ ደሞዝተኛ ደምበኞቹ በወር አጋማሽ ለሚያጋጥማቸዉ የገንዘብ እጥረት 5 መቶ ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ መድቢያለሁ አለ፡፡
ባንኩ "አለኝታ" የተሰኘ የሞባይል የብድር አገልግሎት ማቅረቢያ መተግበሪያ ያስተዋወቀም ሲሆን ለደምበኞቹ ያለማስያዣ ብድር ከ 10 ደቂቃ ባልበለጠ ግዜ ዉስጥ የሚያቀርብበት መሆኑንም አሳውቋል።
የተለያዩ የብድር አገልግሎቶች በዛሬዉ እለት የተዋወቁ ሲሆን ለታክሲ ሹፌሮች እና የሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አፋጣኝ ብድር፣ ለሞባይልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መግዣ ብድርን ጨምሮ ለበጎ ፈቃደኞች የስራ መነሻ እና ሌሎች አገልግሎቶች የብድር አቅርቦት እንደሚያመቻች አስታዉቋል።
በማህሌት አማረ
2023-04-03
