ሀገሬ ቲቪ

3000 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ አምራች ኢንዱስትሪው መቀላቀላቸው ተነገረ፡፡

3000 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ አምራች ኢንዱስትሪው መቀላቀላቸው ተነገረ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 3000 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ማምረት እንዲችሉ መደረጉን አስታውቋል፡፡

ከ81 በላይ አዳዲስ ሼዶች ተሰርተው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

የአምራች ዘርፉ በአማካይ የማምረት አቅም 52 በመቶ በላይ መድረሱ የተጠቆመ ሲሆን የማምረት አቅሙ 80 በመቶ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስቴሩ አማካሪና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አስፋው አበበ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ተዘግተው የነበሩ ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች የነበሩባቸው የተለያዩ ችግሮች ተፈትተውላቸው ዳግም ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉም ተነግሯል፡፡

በወንድማገኝ አበበ
0000-00-00