ሀገሬ ቲቪ

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመትን አፅድቋል።

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛው መደበኛ ጉባኤው ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመትን አፅድቋል።

በተመሳሳይም በምክትል ፕሬዝዳንትነት በእጩነት የቀረቡትን ወይዘሮ ዘሃራ ኡመር አሊን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምፅ ሹመት አፅድቋል።

ሁለቱም ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በናርዶስ ታምራት
2023-04-04