ሀገሬ ቲቪ

ለቀጣዮቹ የትንሳኤ እና ዒድ ዓልፈጥር በዓላት ከ13.6 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ለቀጣዮቹ የትንሳኤ እና ዒድ ዓልፈጥር በዓላት ከ13.6 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ መስከረም ባህሩ እንደገለጹት ለመጪዎቹ በዓላት የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

ከሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ከፊቤላ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት እና ከሸሙ ደግሞ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ለክልሎች ተነግሯል፡፡

በሁለቱ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚገኘውን የምግብ ዘይትም አከፋፋዮች በፍጥነት አንስተው ከበዓላቱ በፊት ለክልሎች ተደራሽ እንዲያደርጉ አቅጣጫ መቀመጡም ተጠቁሟል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-04-04