ሀገሬ ቲቪ

አሳሳቢው ኮሌራ በናይጄሪያ

የዓለም ጤና ድርጅት ናይጄሪያ በዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀው የኮሌራ ወረርሽኝ ተከስቶባታል አለ። ኮሌራንን ለመከላከል የሚደረገው ትግል በክትባት ብቻ የሚሆን አይደለም የንፅህና አጠባበቅን ማሻሻል ተገቢ ነው ብሏል ድርጅቱ።
የናይጄሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዳስታወቀው በ2021 ሀገሪቱ 111 ሺሕ ዜጎች በኮሌራ ተይዘዋል ብሏል። 3ሺሕ600 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም በ2020 ከተመዘገበው የቫይረሱ እና የሟቾች ቁጥር ይበልጣል። በናይጄሪያ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቅረፍ የዓለም ጤና ድርጅት የፌዴራል ዋና ከተማ ግዛትን ጨምሮ በዘጠኝ ክልሎች ውስጥ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት መሰጥቱን ኦል አፍሪካ ኒውስ ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-10