ኢትዮጵያና ጅቡቲ በራሳቸው ገንዘብ የመገበያየት ሙከራ ላይ ናቸው ተባለ፡፡
በኢትዮጵያ ባለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በአገር ውስጥ ገንዘብ የመገበያየት ሙከራ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
ኢትዮጵያ እና የጅቡቲው የመጓጓዣ ንግድ ተቋም በአገር ውስጥ ገንዘብ መገበያየት መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን፤ ይህም የሁለቱን አገራት ንግድና ኢንቨስትመንት ለማቀላጠፍ ትልቅ ዕድል ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አስመጭ እና ላኪዎች አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ ጅቡቲ ውስጥ ለወደብ እና ተያያዥ አገልግሎቶች በውጭ ምንዛሬ ክፍያ ከመፈፀም እንደሚቸገሩ ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-04-04
