
በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ የእንስሳትን ህይወት በመጥፋቱ ነዋሪዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ።
ለ3 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ባለመዝነቡ ድርቁ ሊከሰት ችሏል።
በኦሮሚያ ክልል ኩራ ካሊቻ በተባለ መንደር በመቶዎች የሚቆጠሮ እንስሳት እየሞቱ እንደሆነ ዘኢስት አፍሪካ ዘግቧል።
የየአካባቢው ኃላፊዎችም ነዋሪዎች የከፋ ድርቅ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ተናግረዋል።
ከ100 የሚበልጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በምግብ እጦት አስጊ ሁኔታ ውስጥ በሆስፒታል ይገኛሉ።
ይህ ቁጥር ህፃናትን፣ አዛውንቶችን እና ነፍሰ ጡር እናቶችን ያጠቃልላል ሲል ዘገባው አትቷል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-04-07